አዲስ አበባ ነሀሴ 28/2016 ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት አካል በሆነው የእውቅና እና ሽልማ መርሀ ግብር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል፡፡
እውቅና የተሰጣቸው ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑት የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢኒስቲትዩት፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ስነ ልክ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ አክሪዲቴሽን አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች ሲሆኑ የየተቋማቸውን ተልእኮ ለማሳካት ባስመዘገቡት የላቀ አፈፃፀም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለወጡ አመራርና ፈፃሚዎች ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) የሚኒስትሪያል የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡